ድምጽ-አልባው ዘረፋ፡- በጦርነት ለደቀቀው ህዝብ የፈጠረው ተጨማሪ ችግር
የትግራይ ወርቅ የልማት አቅም ብሎም የእድገት እድል መሆን ሲገባው በጦርነት ለደቀቀው ህዝብ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሚሉት አይነት ተደራራቢ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ከጦርነት ለማገገም እየታገለ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሌላ አሳዛኝ ችግር ቢኖር የወርቅ ዝርፊያ ጧጧፉ ነው፡፡ ጦርነት ባራቆተው ምድር በታች እጅግ አሳዛኝ ክሰተት ራሱን በዚህ መልኩ ይግልጣል ብሎ የጠበቀ አልነበረም፡፡ ይህ የዘረፋ ታሪክ በዘር ጭፍጨፋ ካጣናቸው ነፍሶች በተጨማሪ በህይወት ለተረፈውም ህዝብ የወደፊት እጣ ፋንታ የፈጠረው የችግር ደንቀራ ሆኖ መገኘቱ አስከፊ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፋችን ጦርነት በደቀቀው የትግራይ ክልል ድምጽ አልባው የወርቅ ዝርፊያ እየፈጠረ ያለውን ችግር እንዳስሳለን፡፡
ሁለት ጊዜ አየደማ ያለ ምድር
እንዳለመታደል ሆኖ የትግራይ ምደር ሁለት ጊዜ እየደማ ነው፡፡ አንዴ በጦርነት አረር ሌላ ጊዜ በማዕድን ቁፋሮ፡፡ የትግራይ ምድር ለሁለት አመታት በጦርነት የቀቀቀ መሬት ነው፡፡ መንደሮች ወድመዋል ፡፡ ቤተሰቦች ተዘርፈዋል፡። ብዙዎች ተግድለው የተረፉት ተፈናቅለዋል፡፡ ነገር ግን በሕይወት የተረፉ ሰዎች ሕይወታቸውን ወደ ቀድሞ ሰላም ለመመለስ ሲታገሉ፣ ሌላ አሳዛኝ ነገር አጋጥሟቸዋል። ተስፋ ሊሰጥ የሚገባው መሬት ራሱ እየተዘረፈ የነዋሪዎችን ሰላም እየነሳ ነው ፡፡ እዚህ ላይ ትግራይ የወርቅና የመሰል የከበሩ ማዕደናት ምድር መሆኗ የጥገኞችን ትኩረት እንደትስብ አድርጎ ለዝርፊያ አጋልጧታል፡፡ ይህ ወርቅ እየወጣ ያለው ለትግራይ ህዝብ ሳይሆን ለፖለቲካ ሊህቆች ፣ ለኩባን ባለሀብቶችና ፣ እና በጦርነቱ ሳይቀር ተሳትፎ ለነበራቸው ግለሰቦች ሳይቀር መሆኑ ጉዳዩን ምን ያህልስ የሚያም መሆኑን አመላካች ነው።
ትግራይ ውስጥ ወርቅ ማውጣት ለክልሉ የዕድገት እድል ፣ ለህዝቡ ልማት ሆኖ አልተገኘም፡፡ ይልቁንም ጦርነት ሲሰቃይ ለነበረው ህዝብ ተጨማሪ ቁስል እና ህመም ሆኖ ነው የመጣው፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጀው ሲያሰቃዩት የነበሩ ጠላቶች በትግራይ ህዝብ ትግል ተሸነፈው ምድሩን ለቀቅው ቢወጡም እንደገና በሰላም ሰበብ ተመልሰው ሌላ ስቃይ እየፈጠሩ ነው፡፡ ቀደም ሲል ህዝቡን ሲያሰቃዩ የነበሩ ወራሪዎች አሁን መልካቸውን ቀይረው ባለህበትና የቢዝነስ ሰው መስለው በመምጣት በገዛ በመሬቱ ላይ ሀብቱን እየዘረፉት ነው፡፡ እውነትም የትግራይ ምድር አምና በጦርነት ዘንድሮ ደግሞ በዝርፊያ ሁለት ጊዜ እየደማ ነው፡፡
ለመሆኑ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ለዚህ ዘረፋ ለምን ተመረጠ? ትግራይ የማዕድን ሀብታም ናት ፡፡ ማንኛውም የትግራይ መሬት ቢቆፈር የማዕድን ችግር የለበትም፡፡ ነገር ግን ጥገኞች ለማዕድን ዘረፋ ሰሜን ምዕራብ ትግራይን ለምን መረጡ ካልን ምክንያቱ ኤኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የሰሜን ምዕራብ የትግራይ ክፍል የትግራይ ህዝብ የትግል ማዕከል መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ ህወሓት ትግል የጀመረው ደደቢትና ሽረ አካባቢ ነው፡፡ የትግል ታሪኩ ብቻ ሳይሆን አሁንም ቢሆን ይሄ አካባቢ የትግል ደጀን ሆኖ ነው የሚታው፡፡ ስለዚህ ይሄንን አካባቢ በዘረፋም በወከባም መረበሽ የትግራይ ህዝብ አስኳል እንደመምታት ነው የሚታሰብው፡፡ ጥገኞች እና የትግራይ ጠላቶች እንደሚያስቡት እዚህ አካባቢ ያለው ሶሽዮ-ፖለቲካል መሰረት ማፍርስ ትግራይን ለማንበረክክ አመቺው የኢላማ ቦታ አድርገው ነው የሚመለከቱት፡፡ ስለዚህ ችግሩ የኤኮኖሚ ዘረፋ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ሴራም ጭምር ነው፡፡
ስውር ተዋናዮች
በትግራይ ወርቅ ዘረፋ ላይ ያለው የተወሳሰብ ሰንሰለት እና ስውር እጆች ችግሩን አወሳስበውታል፡፡ ሌባ በአዳባበይ እንዳማይሰርቀው ሁሉ የትግራይን ህዝብ እየዘረፉ ያሉ አካላትም ስውር ተወናዮች ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል ጥቂቶቹን እንመልከት፡፡
የፌዴራል ኃይሎች
የፌዴራል አካል የትግራይ ወርቅ ዘረፋ ህጋዊ ፈቃድ የሚሰጥ ነው፡፡ በዚህም የዘረፋው መስራችና እውቅና ሰጪ ፣ ለብዙዎች አገር ውስጥና ውጪ ዘራፊዎች ፈቃድ በመስጠት ለህገ-ወጥ ዝርፊያው ህጋዊ ሽፋን የሚሰጥ አካል ነው፡፡ በዚህም ባሉት የቢሮክራሲ ተቋማት አማካኝነት ህጋዊ ዘረፋ እንዲሳለጥ በማድረግ የትግራይ ሀብት ከአገር ውስጥ አልፎ ራቅ ያሉ የውጪ አገራት ዘራፊዎች እጅ ላይ እንዲደርስ ዘረፋውም መጠነ ሰፊ እንዲሆን ያደረገ ነው፡፡
የፌደራል ኃይሎች ይህንን ዘረፋ ለማከናወን በትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናትን መድበዋል፡፡ የዚህ የማዕደን ዘረፋ አሳብ አመንጪ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሲሆኑ ይህንን ተልዕኮ ከአዲስ አበባ ይዘው የሚመጡት ደግሞ አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው፡፡ ጄኔራል ፃድቃን በዚህ አይነት የንግድ ዘርፍ የካበተ ልምድ ስላላቸው የስራው አስፈፃሚ ናቸው፡፡ ጄነራል ፃድቃን በተመድ በነበራቸው ተልዕኮ በተጓዳኝ ሲያደርጉት በነበረው ንግድ ላይ ከፍተኛ የሆነ የመዝረፍ ልምድ ያካበቱ ሲሆን በትግራይም ተግባራዊ ያደረጉት ይህንኑ የዘረፋ ልምዳቸውን ነው፡፡
የክልል ጊዜያዊ አስተዳደር
ከጦርነቱ በኋላ በነበረው የሰላም ስምምነት የተመሰረተው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አላማው ጦርነቱ የፈጠራቸውን ችግሮች እየለዩ መፍታት ነበር፡፡ በዚህም ተፈናቃይ የመመለስ ፣ የትግራይ የግዛት አንድነትን ቀድሞ ወደነበረበት ማስመለስ እና መልሶ የማቋቋም ስራዎች ዋንኛ ተግባሩ ነበሩ፡፡ እነዚህን ወደ ጎን በመተው በትግራይ የወርቅ ዝርፊያን በማመቻቸት በኩል የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሚና ላቅ ያለ ነበር፡፡ በዚህ የተላላኪነት ሚና በነበረው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተግባር ከማዕድን ኩባንያዎች ጋር ስምምነቶችን በማመቻቸት፣ ለፌዴራል ጥቅም አማላጅ በመሆን እና ህዝባቸውን እንዲበዘብዙ በማድረግ ተባባሪ ነበር ፡፡
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የበላይ ሹመኞች የዚህ ዘረፋ የበላይ አስተባባሪዎች ናቸው፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳ ከፌዴራል ነጋዴዎች ጋር የንግድ ግንኙነቱን ሰንሰለት አያያዥ ሆነው የተላላኪነትም የደላላነትም ሚና ይወጫወታሉ፡፡ በእሳቸው ስር የቅርብ ወዳጆቻቸው ዘረፋው ላይ እጃቸውን ከትተው ኪሳቸውን እንዲያደልቡ ይደረጋል፡፡ አቶ ጌታቸው በዚህ መልኩ በቅርብ ሰዎቻቸው በኩል እየነገዱ ለፌዴራል አለቆቻቸውም የዘረፋ እድል ያመቻቻሉ፡፡ ጄኔራል ፃድቃን እዚሁ ላይ በተመሳሳይ የራሳቸው የዘረፋ ሰንሰለት ፈጥረው ከላይ እስከ ታች ያለውን የንግድ መስመር የተቆጣጠሩ ናቸው፡፡ ጥይት ራሱ ተኩሶ ራሱ ይጮሀል እንደሚባለው ሚዲያውን በመቆጣጠር ራሳቸው የሰሩትን ጥፋት በሌላ በማላከክ ይጮሀሉ ፡፡ በዚህም ርካሽ የሆነ የመንጋ ድጋፍን ለመፈጥር ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
የቀድሞ ታጣቂዎች እና ወታደራዊ መሪዎች
የትግራይ መከላከያ ሰራዊትና መሪዎች ትግራይ የተጋረጠባትን የህልውና አደጋ የቀለበሱ መሆናቸው አይካድም፡፡ ያም ሆኖ አንዳንዶች የቀድሞ ተዋጊዎችና ወታደራዊ አመራሮች አሁን ወርቅ በማውጣት እጃቸውን አስገብተው ታዝበናል። በዚህም በወታደራዊ መሪዎችና ሰራዊታቸው በመታገዝ የማዕድን ስራዎችን በብረት መዳፍ መቆጣጠርና ህጋዊ አካሄዶችን በሀይል የመቀልበስ እዚህ ጉዳይ ላይ ፍርሀት በማንገስ በማከናወን የወርቅ ዝርፊያው ላይ ድርሻ ነበራቸው፡፡ በዚህም እነዚህ የቀድሞ ተዋጊዎችና ወታደራዊ መሪዎች በትግራይ በትግል ያገኙትን ወታደራዊ አቅም በመጠቀምና በአካባቢው ባለስልጣኖች እየተደገፉ ችግሩ እንዲስፋፋ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡
አቶ ጌታቸው ስልጣኑን እንደተቆጣጠሩ ህወሓትን ለሁለት ለመክፈል ነው የሞከሩት፡፡ ይህንን ለማድረግም በህወሓት ውስጥ የነበሩ የመጠጥ ጓደኞቻቸውን ይዘው ወጡ፡፡ ይሄ ግን ህወሓትን ሊያደክመው ባይችልም ሌላ መዋቅር ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ለአቶ ጌታቸው ተሞክሮ መሆኑ አልረቀም ፡፡ ይቺን ሞዴል ተክተለው የትግራይን መከላከያም ለሁለት ለመከፍል ሞክረዋል፡፡ ለሁለት መክፈል ባይችሉም ግን በሰራዊቱ ውስጥ የራሳቸው የሆኑ ተላላኪ የሚሆኑ ጥቂትና በጣት የሚቆጠሩ ወታደራዊ መሪዎች አላጡም፡፡ እነዚህን ወታደራዊ መሪዎችን ነው አንግዲህ ለማዕደን ዘረፋቸው ዘብ አድርገው የተጠቀሙት፡፡
የአካባቢው አስተዳደር
በየደረጃው ባሉ የመንግስት መዋቅሮች ማለትም ከቀበሌ እስከ ወረዳ እስከ ዞን ድረስ ያሉ የአካባቢው ባለስልጣናት በዚሁ በወርቅ ዘረፋ ወሳኝ ሚና ሲጫወቱ ነበር የሚል ወቀሳ ተነስቶባቸዋል፡፡ ይህ ተራ ወቀሳ ግን መሬትም ላይ በተግባር የታየ በመሆኑ እውነትነት አለው ፡፡ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ያላቸውን የቢሮክራሲ አቅም ተጠቅመው ለህገ-ወጥ ዘረፋ ፈቃዶችን ይሰጣሉ፣ ስራዎችን ያጸድቃሉ እና ለብዝበዛ መንገዱን ያስተካክላሉ። ለአብዛኞቹ እነዚህ ባለስልጣናት ከጦርነቱ በኋላ ባለው ኢኮኖሚ ውስጥ ህገወጥ ዝርፊያ ላይ መሳተፍ ማህበረሰባቸውን መክዳት ቢሆንም እንኳ የጥቅም ጉዳይ በመሆኑ የበኩላቸውን ከመውሰድ ወደ ኋላ እንደማሉ አይተናል፡፡
አቶ ጌታው በምክር ቤት የተመሰረተ ህጋዊውን የመንግስት መዋቅር በማፍረስና ማህተም በማሻሻል የታችኛውን እርከን ወደ ራሳቸው እጅ አስገብተው ነበር፡፡ እነዚህ በአዲስ መልክ የተዋቀሩት የአቶ ጌታቸው ረዳ የቀበሌና ወረዳ ካድሬዎች የማዕድን ዘረፋ ስራውን እየተላላኩ ያስፈጽማሉ፡፡ እነሱም ከሚተራርፈው ሽርፍራፊ ተጠቃሚ ሲሆን የአቶ ጌታቸው ረዳ ስብስብ ከፊሉን ወስዶ ከፊሉ ደግሞ ለአብይ አህመድ ይላካል፡፡ ይህንን የወርቅ ዘረፋ እነሱ መንግስት ሆነው ስለዘረፉ ብቻ ህጋዊ ንግድ ነው ብለው ጠሩታል፡፡ እውነታው ግን ዘረፋ ነው፡፡
ኩባንያዎች
በዚህ አሳዛኝ ክስተት ሌሎቹ ተሳታፊዎች በክልል ፣ በፌዴራል እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የንግድ ተቋማትና ኩባንያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥም ወደ ክልሉም የሚገቡት በኢንቨስትመንት ፈቃድ በጤነኛ ልማት ላይ ለመሳተፍ ቢሆንም ጥገኛ የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ከተፈጠረ ግን የእድላቸውን ይሞክራሉ፡፡ በትግራይም በዚሁ መልኩ በተፈጠረላቸው ደካማ የመንግስት ቁጥጥርና ጥገኛ ፖለቲካ የተነሳ በወርቅና መሰል የሀብት ዝርፊያ ላይ በስፋት ተሰማርተዋል፡፡ ከመንግስት መዋቅሩ ጋር በፈጠሩት ጥገኛ ትስስር የትግራይን ሀብት ሲዘርፉና ሲያግዙ በመቆየታቸው ከሌላው ባልተናነሰ መልኩ የችግሩ ባለድርሻ ናቸው፡፡
የወርቅ ፈቃድ የመስጠት ስልጣን ያለው የፌደራል አካል ነው በሚል ሰበብ አብዛኛዎቹ ኩባንያዎች አብይ አህመድ ፈቃድ ወደ ትግራይ የተላኩ ናቸው፡፡ ከአብይ አህመድ የተላኩበት ምክንያት ደግሞ የንግድ ሸሪክ ስለሆኑ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ የራሳቸው የጠቅላይ ሚሩ የድብቅ የዘረፋ መሳሪዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች አቶ ጌታቸው ረዳን ፣ ጀኔራል ፃድቃንን ከመሳሰሉ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሹማምንቶችም ጋር የንግድ ሽርክና ያላቸው በመሆኑ እንደ ልብ እንዲዘርፉ መስመሩ የተመቻቸላቸው ናቸው፡፡
የብዝበዛው ስልት
የወርቅ ማውጣት ስራዎች የኤኮኖሚያዊ ጉዳይ ብቻ አይደሉም ፡፡ ጉዳዩ ፖለቲካዊም ወታደራዊም መልክ ያለው ነው፡፡ የንግድ ተቋማት እንደሚሰታፉበት ሁሉ ፖለቲከኞችና የወታደራዊ መሪዎችም እጃቸውን ያስገቡበት ጉዳይ ነው፡፡ የብዝበዛው ስልት ዝርፊያው ላይ ያሰፈሰፉ አካላትን አሰላልፍ መነሻ የሚያደርግ ሲሆን ፖለቲከኞችን ዝርፊያውን ያስተባብራሉ፡፡ ታጣቂዎችና ወታደራዊ መሪዎች ዝርፊያውን ያጅባሉ፡፡ በዚህም ህጋዊ ተጠያቂነትና የመንግስት ሀላፊነት እንዲዳከም በማድረግ ዝርፊያውን እንዲሳለጥ ያድርጋሉ፡፡
የመንግስት መዋቅሩ ወይ ሽባ ነው ወይም እሱ ራሱ በዝርፍያው ተሳታፊ በመሆኑ ህገ- ወጥ ድርጊቱን መከላከል የሚችልበት ፖለቲካዊ አቅም የለውም፡፡ አብዛኛውም አካባቢ ላይ የመንግስት መዋቅሩ በዘራፊዎች እጅ ላይ በመውደቁ የዘርፊያው መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡
መሀል ላይ ዝርፊያው የፈጠራቸው ደላሎች የተለያዬ መልክ ይዘው ተፈጥረዋል፡፡ አቀባባይ ብቻ ሳይሆኑ የብዝበዛውን ስልት እየቀየሱ የዝውውር ስርዓቱን የገነቡ ናቸው፡፡ ከየት ወዴት እንደሚንቀሳቀስ እያቀዱ ይተገብራሉ፡፡ በዚህም የትግራይ ወርቅና ሀብት የሚበዘበዘው በኮንትሮባንድ ድንበር ተሻግሮ ኤርትራ እና ዱባይ ቁልፍ ድረስ ባለው የበዝዝዛ ሰንሰለት ነው፡፡
የሰብአዊ ዋጋ
የእዚህ ብዝበዛ ዋጋ የሚለካው በጠፋው ሀብት ብቻ ሳይሆን በሰዎች ስቃይ ነው። ወርቅ የሚወጣባቸው ማህበረሰቦች ከመኖሪያቸው መፈናቀል፣ የአካባቢ ውድመት እና የድህነታቸው መባባስ ምክንያት ሆኗል፡፡
አንድ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ነዋሪ አርሶ አደር ቤተሰቦቻቸው እንዴት መሬታቸውን ለቅቀው በማዕድን ፍለጋ ምክንያት የተፈጠረባቸውን ችግር ሲገልጹ፡-
"ለልማት ነው ብለውናል ነገር ግን ምንም ነገር አላየንም - ካሳ፣ ስራ የለም፣ ተስፋ የለንም ፣ ያለው መሬታችንን የሚገነጣጥል የማሽን ድምፅ ብቻ ነው።" ብለዋል፡፡
ከዘር ማጥፋት ጦርነት የተረፉት ቤተሰቦች፣ የወርቅ ማውጣቱ እንደ ሁለተኛ የጥቃት ማዕበል ሆኖ ይሰማቸዋል። ከወርቅ ዘረፋ ጎን ለጎን ያለው የትግይ ገጽታ አስከፊ ነው፡፡ ሕጻናት የሚራቡባት፣ ትምህርት ቤቶች የፈራረሱባት፣ ንጹሕ ውኃ በምትሆንባት ምድር፣ የልማት ተስፋዎች የተሟጠጡባት አገር ከወርቅ ቁፋሮው ጀርባ ያለ አሳዛኝ እውነታ ነው።
የእምነት ክህደት
ምናልባት የዚህ አሳዛኝ ክስተት በጣም የሚያሠቃየው ነገር የትግራይን ህዝብ መጠበቅ ያለባቸው ሰዎች የእምነት ክህደት ነው። ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣የአካባቢው ባለስልጣናት እና የቀድሞ ታጣቂዎች ሳይቀር ክልሉን መልሶ መገንባት የሚገባቸው ግለሰቦች በሙሉ እንደልባቸው ከሚበዘብዙት ጋር ተሰልፈው ማየት የሚሳዝን ነው፡፡
ይህን ክህደት ያስተዋሉ አንድ አዛውንት እንደሚሉት ከሆነ "ከዚህ በፊት ብዙ አጥተናል-ቤታችንን፣ የምንወዳቸውን ሰዎች። አሁን ከእግራችን በታች ያለው መሬት እንኳን እየተሰረቀ ነው።" በሚል አሳባቸውን በሀዘን ስሜት ገልፀዋል፡፡


Comments
Post a Comment