ድምጽ-አልባው ዘረፋ፡- በጦርነት ለደቀቀው ህዝብ የፈጠረው ተጨማሪ ችግር
የትግራይ ወርቅ የልማት አቅም ብሎም የእድገት እድል መሆን ሲገባው በጦርነት ለደቀቀው ህዝብ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሚሉት አይነት ተደራራቢ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ከጦርነት ለማገገም እየታገለ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሌላ አሳዛኝ ችግር ቢኖር የወርቅ ዝርፊያ ጧጧፉ ነው፡፡ ጦርነት ባራቆተው ምድር በታች እጅግ አሳዛኝ ክሰተት ራሱን በዚህ መልኩ ይግልጣል ብሎ የጠበቀ አልነበረም፡፡ ይህ የዘረፋ ታሪክ በዘር ጭፍጨፋ ካጣናቸው ነፍሶች በተጨማሪ በህይወት ለተረፈውም ህዝብ የወደፊት እጣ ፋንታ የፈጠረው የችግር ደንቀራ ሆኖ መገኘቱ አስከፊ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፋችን ጦርነት በደቀቀው የትግራይ ክልል ድምጽ አልባው የወርቅ ዝርፊያ እየፈጠረ ያለውን ችግር እንዳስሳለን፡፡ ሁለት ጊዜ አየደማ ያለ ምድር እንዳለመታደል ሆኖ የትግራይ ምደር ሁለት ጊዜ እየደማ ነው፡፡ አንዴ በጦርነት አረር ሌላ ጊዜ በማዕድን ቁፋሮ፡፡ የትግራይ ምድር ለሁለት አመታት በጦርነት የቀቀቀ መሬት ነው፡፡ መንደሮች ወድመዋል ፡፡ ቤተሰቦች ተዘርፈዋል፡። ብዙዎች ተግድለው የተረፉት ተፈናቅለዋል፡፡ ነገር ግን በሕይወት የተረፉ ሰዎች ሕይወታቸውን ወደ ቀድሞ ሰላም ለመመለስ ሲታገሉ፣ ሌላ አሳዛኝ ነገር አጋጥሟቸዋል። ተስፋ ሊሰጥ የሚገባው መሬት ራሱ እየተዘረፈ የነዋሪዎችን ሰላም እየነሳ ነው ፡፡ እዚህ ላይ ትግራይ የወርቅና የመሰል የከበሩ ማዕደናት ምድር መሆኗ የጥገኞችን ትኩረት እንደትስብ አድርጎ ለዝርፊያ አጋልጧታል፡፡ ይህ ወርቅ እየወጣ ያለው ለትግራይ ህዝብ ሳይሆን ለፖለቲካ ሊህቆች ፣ ለኩባን ባለሀብቶችና ፣ እና በጦርነቱ ሳይቀር ተሳትፎ ለነበራቸው ግለሰቦች ሳይቀር መሆኑ ጉዳዩን ምን ያህልስ የሚያም መሆኑን አመላካች ነው። ትግራይ ውስጥ ወርቅ ...