የጌታቸው የሽንፈት ድምጾች በኢትዮፎረም
ሰሞኑን ኢትዮፎረም የራሱ ያልሆኑ ድምጾችየሚስተጋቡበት የገደል ማሚቶ ሆኖ እያገለገለ ነው፡፡ አቶጌታቸው አክቲቪስት ሆነው በአደባባይ በየ-ዩቱዩቡ ያሰራጩትአሉባልታ አልበቃ ብሏቸው አሁን ደግሞ በታዋቂ ዩቱዩብ ጀርባብቅ ያሉ ይመስላሉ፡፡ ቀድሞ ከትግራይ ህዝብ ጎን ተስልፎድምጹን ሲያሰማ የምናውቀው ኢትዮፎረም አሁን ደግሞ በትግራይ ህዝብ እና በመሪው ድርጀት ላይ የተነሳ ይመስላል፡፡ በሚንስተርነት ማዕረግ የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ ሆነውተሾሙ የተባሉት አቶ ጌታቸው የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ ሆኖ መሾም ማለት ትግራይን መበጥበጥ እንደሆነ “የትግራይንጉዳይ አልጨረስኩም” በሚል በሰጡት አሳብ ነግረውናል፡፡
አቶ ጌታቸው ማልያ ቀይረው ፣ በአዲስ ለተሰለፉበት ሜዳሊጫወቱ ፣ በኢትዮፎረም ጀርባ ያስተጋቡትን ድምፅ ከንቱጩኸት ሆኖ ቢገኝም የሚናቅ ግን አይደለም፡፡ እናም አልፎአልፎ የተወሰነውን አይተነዋል፡፡
ኢትዮፎረም ከወገንተኝነት ፀድተው አስተያየት የሰጡኝያላቸው በግልጽ ስማቸው እነአቶ ጌታቸው ናቸው፡፡ ምክንያቱምየቀረበው አመክንዮ በአብዛኛው የተሸናፊዎች ድምጽ ነው፡፡
ጦርነቱን ከብልጽግና ወደ ህወሓት በማምጣት ፣ ወንጀሉን ከገዳይ ወደ ሟች ፣ በዳይን እየተከላከሉ ተበዳይተበዳይን የወቀሱበት የሚያስተዛዝብ አሳብ ነው፡፡ ይህ ቀደምብለውም መቀለ እያሉ ችግሩ የእኛ ነው በሚል ወደ ህወሓትለማላከክ ያደርጉት የነበረው ጥረት ተቀጥያ ነው፡፡
ድሮ ድሮ አለቃቸው አብይ አህመድ ኢህአዴግን ሊያፈርሱሲሉ መጀመሪያ ያደረጉት ኢህአዴግን በአደባባይ ማንቋሸሽመሆኑን እናስታውሳለን፡፡ 27 አመት ጨለማ ነበር፣ ኢህአዴግአሳሪ ነበር ፣ እንደዚህ ነበር ፣ እንደዚያ ነበር እያሉ ኢህአዴግንሲኮንኑ ከቆዩ በኋላ ኢህአዴግን አፈረሱት፡፡ እነ አቶ ጌታቸውምመቀለ እያሉ ጥፋትን ወደ ህወሓት ያላክኩ ነበር፡፡ አሁንኢትዮፎረም ላይ እየሰማነው የነበረውም ጦርነቱን ወደህወሓት የማላከክ አባዜ ብልጽግናን ከተጠያቂነት ነፃ አድርጎ ህወሓትን የማፍረስ ጅማሬ መሆኑ ገብቶናል፡፡
አቶ ጌታቸው ደብረፅዮን ጥላልኝ ፣ ህወሓትን አንቋሽልኝብለው ለኢትዮፎረሞች የነገራቸው ነው የሚመስለው ፡፡ ህወሓትን በማስረዳትም በመረዳትም ልክ ነው ብሎ ስህተትመንቀስ ምን የሚሉት ነው?ህወሓት ከአዲስ አበባ መምጣትአልነበረበትም፣ስልጣን ለኦሮሞ መስጠት አልነበረበትም እያለንያለው ከእነሽመልስ አብዲሳ ጋር የሚውለው አቶ ጌታቸው ነው ፡፡
አቶ ጌታቸው በኢትዮፎረም አብሮ ያቦካውን እነሱ ብቻይጋግሩት የሚል ነው የሚመስለው ያሉ አሳብ ሰጪዎች ይሄ ሁሉችግር ላይ ጌታቸውም ነበረበት የሚሉ አሉ፡፡ እናም የምስራቅአፍሪካ ጉዳይን የማማከር ስራ ትግራይን ከማተራመስ ሙከራተጀምሯል፡፡ ይሳካል አይሳካም የሚለው ጊዜ የሚፈታውይሆናል፡፡ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል እንደሚባለውበኢትዮፎረም የተሰማው ጩኸት የማን እንደሆነ ገብቶናል፡፡

Comments
Post a Comment