ያልተነገሩት የፃድቃን ኩነኔዎች By Known Unknown
እንደ ፃድቃን አይነት ከተግባሩ በላይ ስሙ የገነነ ሰው ሲያጋጥመው መልከ ጠፉ በስሙ ይደገፉ ይላል የአገሬ ሰው፡፡ ተግባራቸው መጥፎ ሆኖ ለዘመናት በስምና ዝና ስር ተደብቀው ፣ መጥፎ ምግባራቸው የህዝብ ጥቅምና አገር የጎዳ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል ጄኔራል ፃድቃን አንዱ ናቸው ቢባል ማን ያምናል? ጄኔራሉ በቅርቡ ከመቀለ ከሸሹ በኋላ በየሚዲያው እየተጣዱ የባጥ የቆጡን መቀባጠር ጀምረዋል፡፡ የእሳቸው ኩነኔን ደብቀው እንደ ስማቸው ፃድቅ መስለው እየታዩ ያሉት ጄኔራል ፃድቃን የትግል ታሪካቸው የሚያሳየው ግን ብዙ ሰው ከሚገምተው የተለዬ ነው፡፡ ዛሬ ላይ በብልጽግና ጉያ ስር ሆነው የቀድሞ የትግል አጋሮቻቸውን እንከን እየፈለጉ በአደባባይ ለማስጣት የሚሞክሩት ጄኔራሉ በታሪካቸው የፈጸሙት እጅግ አስከፊ ኩነኔ የተሸፈነላቸው ለትግራይ ህዝብ ትግል ሲባል ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ብዙ ሰው የማይገምተውን ያልተሰሙ እና የጀኔራሉን የተበላሸ የትግል ገጽታ የሚያሳዩ ድብቅ ታሪኮችን እንነገራችኋለን፡፡ በጽሞና እንድታነቡት እንጠይቃለን፡፡
በትግራይ ህዝብ ትግል ላይ ጥገኛ ሆነው የበቀሉበት የጄኔራሉ ፃድቃን ኩነኔ የሚጀምረው አሁን ሳሆን የቆዬ መሆኑን ግለሰቡን በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡ በዚህም የጄነራል ፃድቃን የባንዳ ባህሪያቸው የጀመረው ገና ከትግሉ ጊዜ አንስቶ የነበረ ሲሆን በ70ዎቹ የበረሀ ትግል ወቅት ከአሜሪካ የስለላ ተቋማት ጋር ግንኙነት እንደጀመሩ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡ ወደ ኋላ ላይ ይሄ የባንዳ ግንኙነት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ጎልቶ በመውጣት ከሻዕቢያ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የጀኔራሉ የአሜሪካ ተላላኪነት በጽኑ መሰረት ላይ አረፈ፡፡ ያኔ ጀኔራል ፃድቃን ካርሎስ ታላሪኮ (Carlo Talarico) ከሚል ስም ውጪ ምንነቱንም ማንነቱም ብዙም ከማይታወቅ የአሜሪካ ሰላይ ጋር ይተዋወቁና ለባንዳነት ያጠምቃቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ጄነራል ፃድቃን በአደባባይ በአፋቸው ስለኢትዮጵያ እያወሩ እየደሶኩሩ በድበቅ ተግባራቸው ግን ለአሜሪካ ለማገልገል ኤጀንሲ ከፍተው ታማኝነቱን ለማግኘት መስራት ጀመሩ፡፡
ከቀድሞ የኢህዴግ ጥገኛ የአሁን የብልጽግና ሰዎችም ጋር የነበራቸው ትውውቅ ያኔ የተመሰረተ እንጂ ዛሬ እንደ አዲስ የተጀመረ እንዳልሆነ የሚናገሩት እሳቸውን በቅርብ እንደሚያውቋቸው ይናገራሉ እኝህ ሰዎች ዛሬ ጄኔራሉ ብልፅግና ጉያ ገብተው ለመኖር የልብ ልብ የተሰማቸው ግንኙነታቸው የአሁን ሳይሆን የቆዬ ስለሆነ በፈጠሩት አመኔታ እንደሆነ ያስታውሱታል፡፡ በወቅቱ አብይ አህመድ በባድመ ጦርነት ወቅት የውጊያ መሪ የነበረ የአንድ ታጋይ ሬድዮ ኦፕሬተር እያለ ጀኔራል ፃድቃን ጋር የቅርብ ትውውቅ እንደነበረው እማኝነታቸውን የሚያስቀምጡ ውስጥ አዋቂዎች ጄነራል ፃድቃን እና አብይ አህመድ ቡድን ላይ በመስራችነት ሳሙራ የኑስም እንዳሉበት ይናገራሉ፡፡
እነ ጀኔራል ፃድቃን የያኔው የቀጠናው የአሜሪካ ሰላይ ከሆነው ካርሎስ ታላሪኮ (Carlo Talarico) ጋር እየተገናኙ በድጋፍ ሰበብ አቅጣጫም ስምሪትም ይቀበሉ ነበር፡፡ ነጥቦቹን እየገጣጠመን ስንሄድ ይህ ካርሎስ ታላሪኮ (Carlo Talarico) የተባለው የአሜሪካ ሰላይ ደግሞ በጠ/ሚር ኃለማሪያም ወቅት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልኡክ የነበረውና ኢትዮጵያን አፍረሶ ለዚህ ችግር የዳረጋት የዶናልድ ያማማቶ የቅርብ ሰውና የስራ ተባባሪ መሆኑ ጋር ይወስድናል፡፡
ጄነራል ፃድቃን በአንድ በኩል አሜሪካኖቹ የሚሰጧቸውን ተልዕኮ ማስፈጸምና በሌላ በኩል ደግሞ የጦር መሳሪያ ንግዳቸውን ማጧጧፋቸውን ቀጠሉበት፡፡ በዚህ መሀል ደግሞ አብይ አህመድን እያሰለጠኑ ተናካሽ ውሻ ለማድረግ ስራቸውን ሲሰሩ እንደበር የሚያውቁ ሰዎች አብይ አህመድ ሴረኛና ክፉ ፖለቲከኛ ሆኖ እንዲቀረጽ ገና ከጅምሩ የፃድቃን አስተዋጻኦ አለበት ይላሉ፡፡ በወቅቱ በጀመሩት የጦር መሳረያ ንግድ ላይ ተተኳሽ ጥየት በኪሳቸው ይዘው በመዞር ከመሸጥ አንስቶ ትላልቅ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች በመቸብቸብ ሀብት ማከማቸት ጀመሩ፡፡ በዚህ መሀል ደግሞ የሎጅስቲክ አስተባባሪ ሆነው በመመደባቸው ለጦር መሳሪያ ንግዳቸው የተመቻቸ እድል ፈጠረላቸው፡፡ ይሄንንን ሰፋ አድርገው በማስቀጠል አለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ንግድ ውስጥ የገቡት ጄነራል ፃድቃን ወደ ኋላ ላይ ስዬ አብርሃምና አሁን አብረዋቸው በሚደያ የሚቀባጥሩትን የስዬ አብርሃም ወንድም አሰፋ አብርሃም ጋር በመሆን የጦር መሳሪያ ንግዳቸውን ሲያጧጥፉት ነበር፡፡
የአሁኑ አዲስ አበባ ያለው የሚደያ ኔትወርክ የተፈጠረው ያኔ በገነቧት የንግድ ሽርክና መሆኑን የሚናገሩ ሰዎች ጉዳያቸው ከህወሓት ጋር የሚያገናኘው ነገር የወሬ ማጣፈጫ ለማድረግ ብቻ ነው ይላሉ፡፡
ከዚያም በኋላ የተመድ ተልዕኮ የፈጠረላቸውን እድል እየተጠቀሙ በደቡብ ሱዳን ጁባ ፣ በላይቤሪያ ሳይቀር መሳሪያ ሲቸበችቡ ነበር፡፡ እዚህ ላይ የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት የነበረውና ወዲ መቀለ የሚባለው የሻዕቢያ ሰላይ ሳይቀር አብሯቸው ይሰራ ነበር የሚሉት ውስጥ አዋቂዎቹ ዛሬ ጀኔራል ፃድቃን በሚዲያ ወጥቶ የህወሓትና የTDF መሪዎችን በንግድና በዘረፋ ሲከስ ማየት አስቂኝ ሆኖ እንዳገኙት ይናገራሉ፡፡ የጄነራል ፃድቃን ኩነኔዎች ተዘርዝረው አያልቁም የሚሉት እኝሁ ውስጥ አዋቂዎች አብይ አህመድን የአሁን ስሪት ሳይሆን ገና ድሮ ጄነራል ፃድቃን የፈጠሩት ሰው መሆኑንና በዚህ ላይ አሰፋ አብርሀምን የመሰሉ ዘራፊ እየቀረጹ ብዙ አምባገነንና የሌባና ቀማኛ የዘራፊ ቡድን እየገነቡ የነበሩ ሰው ናቸው ይሏቸዋል፡፡
ጄነራል ፃድቃን ያሰመሩላቸውን የዝርፊያ መስመር ተከትለው መዝረፍ የቀጠሉት አቶ አሰፋ አብርሀም በትግራይ ጦርነት ወቅት ለትግራይ ህዝብ የህልውና ትግል ፣ ለተራቡ ተፈናቃይ የትግራይ ተወላጆች እህል መግዣ ተብሎ ከትግራይ ህዝብ በተለይ ከዲያስፖራ የተወጣጣን 300 ሚሊየን ብር ከቻይና ግዢ ጋር በማገናኘት እንክት አድርው የቆረጠሙ አኝህ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ በዚህም ከ300 ሚሊየኑ ጋር አንድ ላይ ህወሓት የሰጣቸውን እምነት የበሉ ሰው ናቸው፡፡ ከአቶ አሰፋ ጋር በዚሁ የህዝብን ሀብት የመጋጥ የረጅም አመታት ልምድ ያላቸው በነ አቶ በየነ መክሩም 300 ሚሊየኑን ጨምሮ ከትግራይ ህዝብ ሀብት ላይ የድርሻቸውን የዛቁ ቀማኛ ናቸው፡፡
አሁን ወጥተው እየቀባጠሩ ያሉትም እንደ ጀኔራሉ ጉዳያቸውን ደብቀው ንጹህ መስለው ለመታየት ቢሆንም እሳቸውም ብዙ ኩነኔ ያለባቸው ሰው ናቸው፡፡
ብዙ ሰው አቶ አርከበ ዝም አሉ፣ የት ሄደው ነው በሚልበት በዚህ ሰባት የነውጥ አመታት ብዙዎች የሚገምቱት አቶ አርከበ ገለልተኛ ሆነው ስራቸውን ብቻ የሚሰሩ ነበር የሚመስለው፡፡ ነገር ግን አቶ አርከብ በዝምታ ወደ ትግራይ እየተኮሱ ነበር፡፡ የአቶ መለስን የልማታዊ መንግስት ፍልስፍና ወደ እንግሊዘኛ እየቀየሩ (እየተረጎሙ ቢባል ይቀላል) ከፈረንጆች ጋር ለመተዋወቅና ዶላር ለማፈስ የቻሉት አቶ አርከበ በዝምታቸው ምሽግ ውስጥ ሆነው በትግራይ ህዝብ ላይ የተኮሱት የባንዳ ጥይት ብዙ ነው፡፡ አቶ አርከበም እንደ ፃድቃን ከአሜሪካኖቹ ሰላዮች ጋር በተለይም ደግሞ ከላይ ስሙን ካርሎስ ታላሪኮ (Carlo Talarico) በሚል ካነሳነው የአሜሪካ ሰላይ ጋር የቅርብ ትውውቅ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሲሆን እንደ እጃቸው መዳፍ የሚያውቋትን የትግራይን መረጃ ለጠላቶች አሳልፎ በመስጠትና ድምጹን አጥፍቶ ወደ ትግራይ ተኩሶ በማስተኮስ አደገኛ ሰው ናቸው፡፡ የፃድቃን የጥገኝነት ቡድን አባል የሆኑት አቶ አርከበ የአብይ አህመድ ጦር በዘመቻ ራስ አሉላ ትግራይ ውስጥ በTDF ሲቀጠቀጥ ከምትሸነፍ ብታስወጣው ይሻላል በሚል ያማከሩት አቶ አርከበ ነበሩ የሚሉት ምንጮች በዚህ ግን አቶ አብይ አህመድ ደስተኛ እንዳልነበሩ ይናገራሉ፡፡ ይሁንና አብይ አህመድ ደስተኛ ባይሆኑም አቶ አርከበ ግን ትግራይ ላይ ተሸንፎ ሊጠፋ የነበረውን የብልጽግናን ሰራዊት ከጥፋት አድነውታል ነው የሚባልላቸው፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳ የተሰጣቸውን ስልጣን ተገን አድርገው የብልጽግና ወንጀለኞች ተገቢውን ፍርድ ሳያገኙ በትግራይ ያለው የምርኮኛ ጉዳይ ተደብሰብሶ እንዲያልፍ ሲያደርጉ አቶ አርከበ ደግሞ በድርድር ምርኮኞችን ከትግራይ እንዲወጡ አደረጉ በማለት ክህደቱ ባጣም የተቀነባበረ ነው የሚባለው ለዚህ ነው በሚል ይከራከራሉ፡፡
ከሁሉም በላይ የሚያስቀው ጀኔራል ፃድቃን ይህን ሁሉ ሲያደርግ አይቶ እንዳላዩ ሆነው ያለፏቸውን የትግል ጓዶቻቸውን ብቻ ሳይሆን ተሸክመው ያኖሯቸውን የTDF አመራሮች ሊገድሉኝ ነበር የማለታቸው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የጄኔራል ጻድቃን ወቀሳ ያልጣማቸው ሰዎች እንደሚሉት ግለሰቡን በቅርብ እንደሚያውቋቸው በህወሓት መሪዎችና ታጋዮች በተደጋጋሚ ከሞት የተረፉ ሰው ናቸው፡፡ በቅርቡ በተደረገው የትግራይ ጦርነት ወቅት በተደጋጋሚ በሻዕቢያ ለመማረክ ቀርበው አሜሪካ እንድታድናቸው ሲማፀኑ ሰሚ ያጡት ጄኔራሉ ለትግራይ ህዝብ ክብር ሲባል ዛሬ የሚወንጀሏቸው ጀኔራል ምግበይ በበረሀ ስሙ ሸሆርተት የሚባለውን ጀግና መድበው ከውርደት እንዳዳኗቸው ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች ይመሰክራሉ፡፡
ጄነራል ፃድቃን በዋልድባ ገዳም ፣ በአዲ መናብር ልዩ ስሙ አምባ ፈሪማ ፣ እንዲሁም ተፋደ ተብለው በሚታወቁ ቦታዎች ተከበው ያደኗቸው ዛሬ ሊገድሉኝ ነበር የሚሏቸው የTDF መሪዎች ናቸው የሚሉት እነዚሁ ምስክሮች ጀኔራል ፃድቃንን መግደል ቢፈለግ ከበረሀ ተሸክሞ ማምጣቱ ለምን አስፈለገ? ፣ ብዙ አጋጣሚዎችን መጠቀም እየተቻለ መስዋእት ከፍሎ እሳቸውን ማዳን ለምን አስፈለግ በሚል መልሰው ይጠይቃሉ፡፡
እነ ጄራል ፃድቃን አዲስ አበባ ተሰባስበው እንደ ልጅ የሚሳዳቡበት ቡድን የተፈጠረው ከፕሪቶሪያ መልስ አይደለም፡፡ ይህ የሚመስለው ብዙ ሰው ሊኖር ይችላል ግን የእነጄኔራል ፃድቃን ፣ አሰፋ አብረሃምና ጄኔራል ሳሞራ ቡድን ከተፈጠረ ረጅም አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ካርሎስ ታላሪኮ (Carlo Talarico) በይፋ የአሜሪካ ተልዕኮውን ለዶናልድ ያማማቶ ካስረከበ በኋላ አሁን እየሰራ የሚገኘው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሆነ ሎጂስትክ ድጋፍ ላይ እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ፡፡
ከዚህ በተጓዳኝ ሺመልስ በሚመራው የአሮሚያ ልዩ ኃይል ውስጥም የተሰጠው ስራ አለው፡፡ እነጄነራል ፃድቃንም መረጃም ተልዕኮም የሚሰጣቸው ከአብይ አህመድ ብቻ ሳይሆን እነሽመልስ ከሚመሩት የአሮሞ ብልጽግና በኩል መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ይሄ ደግሞ እነፃድቃን አሁንም ድረስ አንዴ ለአሜሪካ ሌላ ጊዜ ብልፅግና ፣ በአንድ ጊዜ ለሁለት ሎሌዎች የሚያገለግሉ ሎሌዎች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
ጄኔራል ፃድቃንም ይሁን አሰፋ አብረሃም ወይም በየነ መክሩ ሚዲያ ላይ እየተጣዱ ስለሌላ የሚቀባጥሩት የራሳቸውን ኩነኔዎች ደብቀው ነው የሚሉት ውስጥ አዋቂዎች ይነገር ከተባለማ የጀኔራል ፃድቃንና የጀሌዎቹ ጉድ ይብሳል በሚል ይናገራሉ፡፡ ለምጥዱ ሲባል እንደሚባለው ለትግራይ ህዝብ ክብር ሲባል ገመና አናወጣም ብለን እንጂ በሆዳችን የያዝነው ጉድ ብዙ ነው የሚሉት እነዚህ የቅርብ ሰዎች እንደሚናገሩት በንግድ በዘረፋ እና በፖለቲካ ባንዳነት የተሰማሩት እነዚሁ ሰዎች የራሳቸውን ገበና የማይታወቅና የማይነገር መስሏቸው ስለሌላ ሲተረተሩ ማየት የሚያስተዛዝብ ነው፡፡
በሌላ ጥንቅር እስክንገናኝ ቸር እንስብት፡፡

Comments
Post a Comment