የፃድቃን ምኞት፡- ሻዕቢያን ገድሎ ብልጽግናን ማዳን By Known Unknown

 

ከሰሞኑ በብልጽግና ሚዲያ ብቅ እያሉ ያሉት ጀኔራል ፃድቃን ናቸው፡፡ ከነበሩበት የተከበረ የወታደራዊ አመራር ወደ ተራ የብልጽግና አክቲቪስት እየወረዱ መሆናቸውን የተረዱ ሰዎች ሰቅጥጥ ብሎዋቸው እየታዘቡ ነው፡፡ ምክንያቱም ቀድሞ ይሰጥዋቸው የነበረው ክብር ዛሬ ጄኔራል ፃድቃን ካለቡት ጋር ሲነፀር ሰማይና ምድር ይሆንባቸዋል ጀኔራሉ ከዚህ ነፊት በህዝብ ታጋይነት የሚከበሩ፣ በእውቀታቸው የኮሩ፣ የታፈሩ የተከበሩ ሰው ነበሩ፡፡ አሁን ይህን ግርማ ሞገሳቸውን ገፍው ብልጽግናን ለማዳን በተጠሩበት ሁሉ አለሁ አለሁ እያሉ ይገኛሉ፡፡ ከሰሞኑ የሰጡት ቃለ-ምልልስ ደግሞ ህወሓትና ሻዕቢያን ጥፋተኛ አድርጎ ብልጽግናን ከወንጀል ነጻ የማድረግ አካሄድ ሆኖ ነው በብዙ ሰዎች የታዘቡት ፡፡ እስኪ የጀኔራሉን ቃለ-ምልልስ እኛ እንዴት እንደተረዳነው እንወከሳችሁ፡፡



ጀኔራል ጻድቃን ቃለ-መጠየቃቸውን የሰጡት መጀመሪያ እሳቸውን አድነው ህወሓትን ማጥፋት ላይ ትኩረት አድርገው ነው፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ የባህር በር እንዲኖራት ጥረት እንዳደረጉና በህወሃት በተለይ በአቶ መለስ እረፍ እንደተባሉ ይናገራሉ፡፡ ጀኔራሉ የህወሓትና አቶ መለስን ሃሳቦች በግልጽ እንዳልነገሩን ፣ ከዚህ ይልቅ ስም ለማጥፋት እንዲያመቻቸው የጨማመሩት ነገር እንዳለ ያስተውቅባቸዋል፡፡ በዚህ ንግግራቸው የውሸት ውንጀላዎችን ከማይረባ የምሁር ትንታኔ ጋር ይዘው መጥተዋል ብለው የሚኮንኗቸው አስተያየት ሰጪዎች አላማቸው ማስተካከል ሳይሆን መወንጀል ፣ ስህተት ማሳየት ሳይሆን ማንቋሸሽ በዚህም ብልጽግናን መከላከል ነው ይላሉ፡፡ በዚህም ንግግራቸው ብዙ ነገር እንደሸፋፈኑ ግልጽ ነው፡፡ ያም ሆኖ ኢትዮጵያን የባህር በር ያሳጣት ህወሓት ነው የሚለውን የተለመደ ተራ አሉባልታ ሲያራምዱት ተሰምተዋል፡፡  ይሄ ደግሞ እሳቸውን ንጹህ አድርገው በማቅረብ ተጠያቂው ደግሞ ሌላ የማድረግ ዝንባሌ እንደሆነ ያሳያል፡፡ 


ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በወታደራዊም ሆነ በዴፕሎማሲም ጠነክሮ የወጣበት ወቅት በመሆኑ እሳቸው ይህንኑ የወደብ ጥያቄ ቢያቀርቡም ከአንድ ሰው በቀር የደገፋቸው እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ራሳቸውን ሲያድኑም በተለያዬ ጊዜ ዘመናዊ ትምህርት እንደተማሩና ከዚያ በኋላ ትምህርቱ የወደብ ጉዳይ ከጂኦግራፊያዊ አካሄድ አንፃር በትክክል እንዲረዱ እንዳደረጋቸው በመናገር ለብልጽግና ሲቪያቸውያን የማስገባት ተድርጎ የተቆጠረባቸውን ንግግር አድርገዋል፡፡ ይህ የጀኔራሉ አሳብ አሁን ብልፅግና  ከሚያራምደው የወደብ ጥያቄና የባህር በር አጀንዳ አንፃር ለመላላክ ዝግጁ ነኝ ማለታቸው እንደሆነ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ሰውየው የተላላኪነት ወንበራቸውን ለማጠናከር አስበው ህወሓትን ወንጀለኛ ፣  እራሳቸውን ንጹህ አድርገው አቅርበዋል የሚሉ አሳብ ሰጪዎች ጄኔራሉ እንዲህ ለብልጽግና ተላላኪነት በዚህ መልኩ ይጎመጃሉ የሚል እምነት እንዳልነበራቸው ይናገራሉ፡፡


ጄኔራሉ ሲቀጥሉም ሻዕቢያን ሀጥያተኛ አድርገው ብልጽግናን የማዳን ምኞታቸውን ያንጸባርቃሉ፡፡ በዚህ ንግግራቸው ጄነራሉ ሻዕቢያ ላይ ያልፈጠሩት ጥፋት የለም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ብልጽግና ያጠፋቸውን ጥፋቶች በሙሉ እርሱት የሚል የሚመስል ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚህ በብዙዎቹ ዘንድ መነጋገሪያ በሆነው አሳባቸው ጄኔራሉ የትግራይ ጄኖሳይድ ኮሚሽን ባጠናው ጥናት በአብዛኛው ትግራይ ውስጥ ሰው የገደለው፣ ንጹሀንን ያፈናቀለው፣ ሴቶችን የደፈረው በአጠቃለይ ትግራይን የበደለው ሻዕቢያ ነው ሲሉ የተደመጡ ሲሆን ይሄ ንግግራቸው ብልጽግናን የማዳን ምኞት ተደርጎ ነው የተወሰደባቸው፡፡ በአክሱም የነበረውን ጭፍጨፋ ለሻዕቢያ ሰጥተው ሙሉ ማስረጃ ያለው የማህበረ ዴጎውን እንካን ለብልጽግና ይሰጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ ሁሉንም እጥፍጥፍ አድርገው ለሻዕቢያ በመስጠት የብልጽግናን በደል አለሳልሰው አልፈውታል፡፡ ይሄ እንግዲህ አዲሱ ይብልጽግና አለቃቸውን ጥፋት የመሸፋፈን ምኞት ተደርጎ የሚታይ ሆኖ ተወስዷል፡፡ 


በመጨረሻም መደምደሚያ ያደረጉት የቀድሞ የትግል አጋሮቻቸው የሆኑትን የህወሓት አመራሮች በማጥቃት የብልፅግናን ፖለቲካ የማነቃቃት ንግግር ነው ያደረጉት፡፡ ጦርነቱ ሲጀመር እኔ ተበሳጭቼ ነበር በማለት ራሳቸውን ከደሙ ንጹህ ለማድረግ የሞከሩት ጄኔራሉም ለብልጽግና የገጠምኳችሁ እኔ አይደለሁምና ተቀበሉኝ የሚል አስመስሎባቸዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ጦርነቱን የጀመሩት ህወሓቶች ናቸው ወደሚለው የውንጀላ ክስ የሚሄድ ነው፡፡ 


አንድ  ሚሎቫን ጂላስ ዬጎዝላቪያ ጸሀፊ ያሉትን አሳብ ይዘው መጥተው እንደሳቸው ያፈነገጠ የኮሚኒስት ጸሀፊ እየጠቀሱ የክላስ ምደባ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ወጣት እያለን በኮሚንስት አጀንዳ ተወስውሰን ነው  ወደ ትግል የገባነው እንጂ ተረድተነው አይደለም የሚል እንድምታ ያለው ያለፈው ትግላቸውን እያጣጣሉ የተናገሩት ጄነራሉ አሁን ህወሓት አዲስ ክላስ ሆኖል ወደሚል ውንጀላ ገብተዋል፡፡ ብዙዎች ጄነራሉ ዛሬ ስልጣን ሲያጡ ነው ወይ ይሄ ሁሉ ችግር ትዝ የሚላቸው በማለት ንግግራቸውን አሉባልታ እንደማናፈስ አድርገው ነው የወሰዱት፡፡  


ብዙዎች የጀኔራል ፃድቃንን ንግግር የጦርነት አዋጅ አድርገው ነው የወሰዱት፡፡ በምስራቅ አፍሪካ አስተማማኝ የሆነ ሰላም እንዲሰፍን ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል በማለት የአለቃቸውን ጥያቄ ባገኙት እድል አስተጋብተዋል፡፡ ማንኛውም መንግስት ጦርነትን የፖሊሲ አማራጭ ያደርጋል ያሉት ጄኔራሉ የኢትዮጵያ መንግሰት የወደቡ ጉዳይ በዴፕሎማሲ ካልተሳካ በጦርነት ሊሆን እንደሚችል ግምት አስመስለው ጦርነት አውጀዋል፡፡ በዚህም ይመስለኛል ብለው የተናገሩት አዲሱ አለቃቸው ጦርነት እንደሚፈለጉ ንገርልኝ ብለዋቸው ነው የሚለው የብዙዎች አሳብ ሆኖ ነው ያለፈው፡፡ የጀኔራሉ ንግግር መልሶ መላልሶ ወደብና ባህር በር ላይ እንዲያጠነጥን መደረጉ ጀኔራሉ የብልፅግናን አጀንዳ ይዘው መጡ እንጂ የትግራይ ጉዳይን ማጣፋጫ ከማድረግ ውጪ ሌላ አላማ ይዘው አልመጡም የሚሉ አሳብ ሰጪዎች የጀኔራሉን ንግግር ለአዲስ ጦርነት የተደረገ የፕሮፖጋንዳ ዝግጅት ከመሆን ያለፈው ጥቅም የለውም ይላሉ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

Getachew Reda: The Ultimate Traitor—A Case for High Treason Against Tigray’s Betrayer

ድምጽ-አልባው ዘረፋ፡- በጦርነት ለደቀቀው ህዝብ የፈጠረው ተጨማሪ ችግር

የጌታቸው ክህደት ፡- ከባንዳነት እስከ ተጠያቂነት